Sunday, September 8, 2013

Thursday, September 5, 2013

   “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወር መርሃ-ግብር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)
 “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የ3ወር መርሃ-ግብር በታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል!
 በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
                                                አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ የበለጠ ተጠናክሮ ህዝቡ የትግሉ መሪ ተዋናይና ባለቤትነት እንዲረጋገጥ ላለፉት ሶስት ወራት ፓርቲያችን ባስቀመጠው ስትራቴጂ እቅድ መሠረት ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ሲያደርግ ቆይቱዋል፡፡
በሃገራችን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማለትም ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መረገጥ ፓርቲያችን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል ሰኔ 13ቀን 2005 በይፋ ለጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ፖለቲካዊ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ሕዝባዊ ንቅናቄው በእቅድ መመራት ከመጀመሩ በፊት ሀገራችን የምትገኝበትን ነባራዊ ሁኔታና የህዝባችን ተጨባጭ ኑሮ ላይ ጥናት በማድረግ የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረቡ የፓርቲያችን አብይ ጥያቄ ሆኖ መገኘቱም የንቅናቄውን ወቅታዊነት ያገናዘበ አድርጎታል፡፡
በእቅዳችን መሰረት በመላው ሃገሪቱ ለመጀመሪያው ዙር በተመረጡ ቦታዎች ያደረግናቸው ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በአባሎቻችን፤ በደጋፊዎቻችንና በህዝባችን ጠንካራ ትግልና መስዋእትነት ንቅናቄው የተሳካ ሲሆን ፓርቲያችን ለተከፈለው ዋጋ ሁሉ አድናቆቱን ይገልፃል፡፡
በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመታገዝ የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ ከህግና ሥርዓት ውጪ ማስፈራራት፤ ማሸማቀቅ፤እስራትና ድብደባ በአባሎቻችን ላይ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የቅስቀሳ ቁሳቁስም በአካባቢ የፀጥታ ሰራተኞች ተዘርፈውብናል፡፡ እንዲሁም ህዝብ በነፃ አስተሳሰብ አማራጩን እንዳይከተል በአካባቢ ካድሬዎችና አመራሮች ማስፈራራትና ዛቻ ደርሶበታል፡፡ መርሃ ግብሩም ከተፈፀመ በኃላም ቢሆን ህዝባዊ ንቅናቄውን የተቀላቀሉ ዜጎቻችን በመኖሪያ ቀያቸው ሰርቶ የማደርና በነፃነት የመኖር መብታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡
በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዘብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡ ከህግ ውጭ የገጠሙን መንግስታዊ ተፅእኖዎች ሁሉ ነፃነቱን በተነፈገውና በለውጥ ፈላጊው ህዘባችን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተልኮአችን ሊሳካ ችልዋል፡፡
የሚሊዮኖችን ድምፅ ለማሰባሰብ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያሉ ዜጎቻችን በንቃትና በቁጭት የተሳተፍበት በመሆኑ አመርቂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ፊርማ የማሰባሰቡ መርሃ ግብር የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ መስከረም 5ቀን 2006 በሚደረገው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እስካሁን ካደረግናቸው ህዝባዊ ንቅናቄዎች ልዩ የሚያደርገው የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ይሁንታ ያገኘና ሰላማዊ ሰልፉን በባለድርሻነት የተሳተፉበት መሆኑ ነው፡፡
በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ እስካሁን ካወጣቸው አፋኝ ህጎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተጠናክሮ የመጣውን ህዝባዊ የፖለቲካ ተቃውሞ የበለጠ ለመደፍጠጥ አሳሪ ደንቦች ለማውጣት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተንቀሳቀሰ ለመሆኑ ከገጠመን መልካም አስተዳደር እጦት መገንዘብ ችለናል፡፡
የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የነፃነት ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
                                                     “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”

Tuesday, August 27, 2013

                                                       አንድነት ምሽት
 አጋርነት ለአንድነት የአእላፋት ፊርማ እነሆ የቶሮንቶና አካባቢው ኢትዮጵያዊያን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ወቅታዊ ዘመቻ በመደገፍ የአጋርነት ምሽት አዘጋጅተዋል
ቀን፡ ቅዳሜ ኦገስት 31፡ ከምሽቱ 6 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ 2050 Danforth Avenue፡ ሂሩት የመዝናኛ አዳራሽ
በእለቱ የአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሰይፉ በስካይፕ ንግግር ያደርጋሉ፡ አጫጭር የስነጽሁፍ ስራዎች ይቀርባሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡ በስ.ቁ.፡ 416 422 2962
በኢሜል፡unityforhumanrights@gmail.com

Saturday, August 24, 2013

Thursday, July 18, 2013

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ቀጣይ እቅዱን ይፋ አደረገ

July 18, 2013

የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ዛሬ ሐምሌ 11,2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ የህዝባው ንቅናቄ ዕቅዱን አፅድቋል፡፡
Millions of voices for freedom - UDJበዚሁም መሰረት በሚቀጥሉት የሀገራችን ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቷል፡፡ በየክልሉ ያሉ የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሮች ለፓርቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግብረኃይሉ ያቀዳቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ከአዲስ አበባ አስቀድሞ በክልል ከተሞች ለማድረግ የተወሰነ ሲሆን የህዝባዊ ንቅናቄው ማጠቃለያ የሚሆነው መስከረም አምስት ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይሆናል፡፡ ግብረ ኃይሉ መስከረም 5, 2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀደው ሰላማዊ ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የታሰሩበትን ሁለተኛ አመት ለመዘከር እንደሆነ ታውቋል፡፡
ህዝባዊ ሰብሰባ የሚደረግባቸው ከተሞችና  ቀኖቻቸ
========================
ሐምሌ 21 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ሐምሌ 28 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ሐምሌ 28 ወላይታ ሶዶ
ሐምሌ 28 መቐለ
ነሀሴ 5 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ነሀሴ 26 ድሬደዋ
ነሀሴ 26 አዋሳ
ነሀሴ 26 አምቦ
ነሀሴ 26 ደብረማርቆስ
ህዝባዊ ሰልፎች የሚደረጉባቸው ከተሞች
========================
ሐምሌ 28 ባህር ዳር
ሐምሌ 28 ጅንካ
ሐምሌ 28 አርባ ምንጭ

ነሃሴ 12 አዳማ
ነሃሴ 12 ባሌ
ነሃሴ 12 ወሊሶ
ነሃሴ 12 ፍቼ
ነሃሴ 26 ጋምቤላ
ነሃሴ 26 አሶሳ
መስከረም 5 አዲስ አበባ

Thursday, June 27, 2013


ሕዝባዊ ንቅናቄያችን የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ያደርጋል!!

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት ህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልት በመንደፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን በይፋ መግለጹ አይዘነጋም፡፡ የህዝባዊ ንቅናቄው የመጀመሪያ የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍም ሰኔ 30/10/2005 በጎንደር ከተማ ይደረጋል፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስት በሚደነግገው መሰረትም ፓርቲው ከህዝቡ ጋር የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ማወቅ ለሚገባው አካል የፓርቲያችን መዋቅር አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ ገብተዋል፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ ላይም በጎንደር እየተፈጸመ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ሰዎችን በአደራ ማሰር፣ ለሱዳን ከህዝቡ እውቅና እና ፈቃድ ውጪ መሬት መሰጠቱን፣ በነጋዴዎች ላይ የሚፈጸመውን ኢ-ፍትሃዊ አሰራር፣ ለስራ የደረሱ ወጣቶች የፓርቲ አባል ካልሆኑ በስተቀር ስራ የማያገኙበትን ሁኔታ፣ በዘር ላይ የተመሰረተን ማፈናቀልና የኑሮ ውድነትን አስመልክቶ ህዝቡ የተቃውሞ ድምጹን በነቂስ ወጥቶ ያሰማል፡፡ እንዲሁም የጸረ ሽብር ህጉ የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ በመሆኑ እንዲሰረዝ ይጠየቃል፡፡ ብዙ ሺ የከተማው ኗሪዎችም የተቃውሞ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉን በጎንደር ከሚገኙ የፓርቲው አባላትና አመራሮች ጋር የተሳካ ለማድረግ አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና ቢሮ አስተባባሪ አባላት የተላኩ ሲሆን የቅስቀሳ ስረቸውንም ጀምረዋል፡፡ ቅዳሜም ሁለተኛው ቡድን ወደ ጎንደር ያቀናል፡፡ የፓርቲያችን ስራ አስፈጻሚ፣ የብሄራዊ ምክር ቤትና በየመዋቅሩ ያሉ አባላቶቻችን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ለመገኘት ወደ ጎንደር ያመራሉ፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ጎንደር ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ቅርንጫፍ ቢሮ ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በማምራት በመስቀል አደባባይ በሚደረግ ልዩ ልዩ ፕሮግራም የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ በጎንደር መስቀል አደባባይ ለሚገኘው ህዝብ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦች የሰላማዊ ሰልፉን ዓላማ የሚገልፅ ንግግር ያደርጋሉ፡፡

ፓርቲያችን አንድነትም የሦስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄያችንን ይፋ ካደረግን ጀምሮ ሕዝቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማት፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ የሚዲያ ተቋማት፣ የፀረ-ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ ፔቲሽን ለፈረሙትና ከጎናችን ለቆሙ ታዋቂ ግለሰቦች በአክብሮት ምስጋና እያቀረብን አሁንም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሰኔ 20 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አበባ

Saturday, April 20, 2013

Bureau of Democracy, Human Rights and Labor Country Reports on Human Rights Practices for 2012 Ethiopia

Ethiopia is a federal republic. On August 20, Prime Minister Meles Zenawi died. The ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) elected then deputy prime minister Hailemariam Desalegn to take Meles’s place as chairman of the party. The EPRDF subsequently nominated him for the post of prime minister. On September 21, parliament elected Hailemariam as prime minister. In national parliamentary elections in 2010, the EPRDF and affiliated parties won 545 of 547 seats to remain in power for a fourth consecutive five-year term. Although the relatively few international officials allowed to observe the elections concluded technical aspects of the vote were handled competently, some also noted that an environment conducive to free and fair elections was not in place prior to the election.
Security forces generally reported to civilian authorities; however, there were instances in which special police and local militias acted independently of civilian control.
The most significant human rights problems included restrictions on freedom of expression and association through politically motivated trials and convictions of opposition political figures, activists, journalists, and bloggers, as well as increased restrictions on print media. In July security forces used force against and arrested Muslims who protested against alleged government interference in religious affairs. The government continued restrictions on civil society and nongovernmental organization (NGO) activities imposed by the Charities and Societies Proclamation (CSO).
Other human rights problems included arbitrary killings; allegations of torture, beating, abuse, and mistreatment of detainees by security forces; reports of harsh and at times life-threatening prison conditions; arbitrary arrest and detention; detention without charge and lengthy pretrial detention; a weak, overburdened judiciary subject to political influence; infringement on citizens’ privacy rights, including illegal searches; allegations of abuses in the implementation of the government’s “villagization” program; restrictions on academic freedom; restrictions on freedom of assembly, association, and movement; alleged interference in religious affairs; limits on citizens’ ability to change their government; police, administrative, and judicial corruption; violence and societal discrimination against women and abuse of children; female genital mutilation/cutting (FGM/C); exploitation of children for economic and sexual purposes; trafficking in persons; societal discrimination against persons with disabilities; clashes between ethnic minorities; discrimination against persons based on their sexual orientation and against persons with HIV/AIDS; limits on worker rights; forced labor; and child labor, including forced child labor.
Impunity was a problem. The government, with some reported exceptions, generally did not take steps to prosecute or otherwise punish officials who committed abuses other than corruption.
Factions of the Ogaden National Liberation Front (ONLF), an ethnically based, violent, and fragmented separatist group operating in the Somali Region, were responsible for abuses. Members of the separatist Afar Revolutionary Democratic Union Front (ARDUF) claimed responsibility for a January attack on a group of foreign tourists in the Afar Region.
http://www.state.gov/j/drl/rls/hrrpt/humanrightsreport/index.htm#wrapper

Thursday, January 31, 2013

2013 Human Rights Watch Report (Ethiopia)

January 31, 2013 

የ 2013 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት፡- ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያን ለረጅም ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩትና ሰፊ ስልጣን የነበራቸው መለስ ዜናዊ በነሃሴ ወር በድንገት መሞት በሃገር ውስጥም ሆነ በኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች ዘንድ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ ሽግግር የሚመለከቱ ጥያቄዎችንና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን አስነስቶ ነበር።በኢትዮጵያ ያለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተለይ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ እየከፋ ሄዷል።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በመስከረም ወር ስልጣኑን የተረከቡ ቢሆንም መንግስት በርሳቸው አመራር ሰብአዊ መብቶችን የሚመለከቱ ለውጦች ያደርግ ወይስ አያደርግ እንደሆነ ገና የሚታይ ነው።
እ.ኤ.አ በ2012ም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት መሰረታዊ የሆኑትን ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣ የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብቶች በጥብቅ መገደባቸውን ቀጥለዋል።ለኣሻሚ ትርጉሞች በተጋለጠውና በ2002 ዓ.ም በወጣው የሀገሪቱ የጸረ ሽብርተኝነት ሕግ 30 ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።በዋና ከተማዪቱ አዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል የእስልምና እምነት ተከታዮች ላካሄዷቸው የተቃውሞ ሰልፎች የጸጥታ ሃይሎች የሰጡት ምላሽ የዘፈቀደ አፈሳ፣ እስር እና ድብደባ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግስት በአምስት ክልሎች የሚኖሩ የገጠር ነዋሪዎችን የተሻለ የመሰረታዊ ግልጋሎቶች አቅርቦት ሊያገኙ ወደሚችሉባቸው አካባቢዎች ለመውሰድ በሚል ምክንያት 1.5 ሚሊዮን የገጠር ነዋሪዎችን መልሶ ለማስፈር የሚያካሂደውን የሰፈራ ፕሮግራም ቀጥሎበታል።በጋምቤላ ክልል የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ከፍላጎታቸው ውጭ በሃይል እንዲፈናቀሉ በመደረጋቸው ለከፍተኛ ችግሮች ተጋልጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም መንግስት ለሚያካሂደው ሰፊ የስኳር ልማት መሬት ለማስለቀቅ ሲባል በኢትዮጵያ የታችኛው ኦሞ ሸለቆ ነዋሪ የሆኑትን አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረገ ነው።
ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብቶች

መንግስታዊ ያልሆኑ ደርጅቶችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር  የበጎ አድራጎት ደርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ እንዲሁም የጸረ ሽብርተኝነት ሕግ በ2002 ዓ.ም ከታወጁ ወዲህ በኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ከፍተኛ ገደብ ተጥሎባቸዋል። እነዚህ ሁለት ሕጎች መንግስት በሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች፣በጋዜጠኞች እና በሌሎችም የመንግስትን ፖሊሲ በሚተቹና መንግስት እንዲነሱ በማይፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳባቸውን በሚገልጹ ሰዎች ላይ ካካሄደው ሰፊ እና የማያቋርጥ ማዋከብ፣ዛቻ እና ማስፈራራት ጋር ተዳምሮ ያስከተሉት  ውጤት የከፋ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ የጎላ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች እንቅስቃሴዎቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንሱ ወይም ሰብአዊ መብቶችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከስራ ዝርዝራቸው ውስጥ እንዲያወጡ የተገደዱ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቀ ድርጅቶችም ጭራሹኑ ተዘግተዋል። በደረሰባቸው ማስፈራሪያ ምክንያት ሰፊ ልምድና መልካም ስም የነበራቸው ብዙ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ሃገሪቱን ለቀው ሄደዋል። አሁን ሰፍኖ የሚገኘው ሁኔታ ለነጻ ፕሬስ እንቅስቃሴም እንዲሁ የተመቸ አይደለም።ባለፉት አስር ዓመታት በደረሰባቸው ዛቻ እና ማስፈራራት ሳቢያ ሃገራቸውን ለመልቀቅ በተገደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር በዓለም ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ ናት። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ሲፒጄ እንደሚገልጸው ቢያንስ 79 ጋዜጠኞች ሃገራቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።
የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ፣ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎችን ዒላማ ለማድረግ፣ተቃውሞን ለማፈን እና ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት ስራ ላይ እየዋለ ነው። እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም 30 የፖለቲካ መሪዎች፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እንዲሁም ጋዜጠኞች በግልጽ ባልተብራሩ የሽብርተኝነት ወንጀሎች ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።ከ2011 ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ 11 ጋዜጠኞች በዚሁ ሕግ ተከሰው ተፈርዶባቸዋል።

ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም አሁን የተዘጋው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ በነበረው ውብሸት ታዬ እና የጋዜጣው ዓምደኛ በነበረችው ርዕዮት ዓለሙ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኝ ፍርድ ቤት የ 14 ዓመታት እስር ፈርዶባቸዋል።የርዕዮት ዓለሙ ፍርድ በኋላ በይግባኝ ወደ አምስት ዓመታት የተቀነሰ ሲሆን ከቀረቡባት ክሶች ውስጥም አብዛኞቹ ተሰርዘዋል።
ከፍተኛ ክብር ያለውን የፔን አሜሪካ ፍሪደም ቱ ራይት ሽልማት በሚያዝያ ወር 2004 ዓ.ም ያሸነፈው አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ብሎገር እስክንድር ነጋ ሐምሌ 6 ቀን 2004 ዓ.ም ከሌሎች ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ጋር በቀረበበት ክስ የ 18 ዓመታት እስራት ተፈርዶበታል። በስደት ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች አብይ ተክለማርያም እና መስፍን ነጋሽም እስካሁን ድረስ ጋዜጠኞች ላይ ብቻ ተግባራዊ በተደረገው የጸረ ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀጽ መሰረት ጥፋተኛ ተብለው እያንዳንዳቸው የ 8 ዓመታት እስራት ተፈርዶባቸዋል። በይፋ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚ ፓርቲ አንድነት ለፍትሕ እና ለዲሞክራሲ አባል የሆነው አንዷለም አራጌ በስለላ፣ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በመናድ እንዲሁም የሽብር ተግባር ለመፈጸም ምልመላ እና ስልጠና በማካሄድ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብሎ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።
በመስከረም ወር 2004 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእስክንድር ነጋ እና በስደት ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ አበበ በለው  እንዲሁም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባሉ አንዷለም አራጌ ንብረቶች እንዲወረሱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
 
 click the link for full reporthttp://www.hrw.org/world-report/2013/country-chapters/112447