የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ቀጣይ እቅዱን ይፋ አደረገ
July 18, 2013
የአንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ህዝባዊ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ዛሬ ሐምሌ 11,2005 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀጣይ የህዝባው ንቅናቄ ዕቅዱን አፅድቋል፡፡
በዚሁም መሰረት በሚቀጥሉት የሀገራችን ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና ታላላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ጠርቷል፡፡ በየክልሉ ያሉ የአንድነት ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሮች ለፓርቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግብረኃይሉ ያቀዳቸው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች ከአዲስ አበባ አስቀድሞ በክልል ከተሞች ለማድረግ የተወሰነ ሲሆን የህዝባዊ ንቅናቄው ማጠቃለያ የሚሆነው መስከረም አምስት ቀን 2006ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ይሆናል፡፡ ግብረ ኃይሉ መስከረም 5, 2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ያቀደው ሰላማዊ ታጋዮቹ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የታሰሩበትን ሁለተኛ አመት ለመዘከር እንደሆነ ታውቋል፡፡
ህዝባዊ ሰብሰባ የሚደረግባቸው ከተሞችና ቀኖቻቸ
========================
ሐምሌ 21 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ሐምሌ 28 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ሐምሌ 28 ወላይታ ሶዶ
ሐምሌ 28 መቐለ
ነሀሴ 5 አዲስ አበባ በሁለት ቦታዎች
ነሀሴ 26 ድሬደዋ
ነሀሴ 26 አዋሳ
ነሀሴ 26 አምቦ
ነሀሴ 26 ደብረማርቆስ
ህዝባዊ ሰልፎች የሚደረጉባቸው ከተሞች
========================
ሐምሌ 28 ባህር ዳር
ሐምሌ 28 ጅንካ
ሐምሌ 28 አርባ ምንጭ
ነሃሴ 12 አዳማ
ነሃሴ 12 ባሌ
ነሃሴ 12 ወሊሶ
ነሃሴ 12 ፍቼ
ነሃሴ 26 ጋምቤላ
ነሃሴ 26 አሶሳ
መስከረም 5 አዲስ አበባ