Unity for Human Rights and Democracy is a volunteer based, not for profit community organization, striving to empower Ethiopian-Canadians to advocate for Human Rights,Democracy and Good Governance in Ethiopia.
Thursday, June 30, 2016
Wednesday, June 29, 2016
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ለስራ ጉበኝት ካናዳ ገቡ
አቶ ይልቃል ጌትነት፡ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፤ ለሁለት ሳምንት የስራ ጉብኝት ዛሬ ማክሰኞ፤ ጁን 28 ቀን፤ ካናዳ ገቡ፡፡ አቶ ይልቃል በቶሮንቶ ፒርሰን አለማቀፍ አይር ማርፊ ሲገኙ፤ በከተማው የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ሰጪዎች ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸዋለው፡፡
አቶ ይልቃል፤ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜያት ለስራ ጉብኝት ወደአሜሪካ ሊጓዙ ሲሉ ከቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ያላግባብ በመመለሳቸው፤ ይሄኛው ጉዟቸውም ይስተጓጎላል የሚል ስጋት እንነደበራቸው በስፍራው የተቀበሏቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ፤ በአጭር ግዜ ጥሪ የተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን ለሊቀመንበሩ አቀባበል አድርገውላቸው፤ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በቅርቡ በመገናኛ ብዙሃን የተለያየ ትችትና መጋለጥ የደረሰበት የኢትዮጵያ... መንግስት፤ የአቶ ይልቃል ጉዞ መስተጓጎል ሌላ ትችት ይጋብዛል በሚል ስጋት እንዳሳለፋቸው ነው አስተያየት ሰጪዎች የተናገሩት፡፡
ቶሮንቶ በዚህ ዓመት የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌደሬሽን ውድድር አዘጋጅ ስትሆን፤ ሰማያዊ ፓርቲና አቶ ይልቃል ጌትነት፤ ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች ጋር በመሆን፤ በቶሮንቶና በሌሎች የካናዳ ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችንና የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶችን እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡
አቶ ይልቃል፤ በቅርቡ በፓርቲያቸው ውስጥ ስለተፈጠረው አለመግባባትና ፈተና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል፡፡ ከአቶ ይልቃል ጋር ስለሚኖሩ ዝርዝር ዝግጅቶች በቀጣዮች ቀናት እንደሚገለጡ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)