ሰንደቅ ጋዜጣ ታማኝ ምንጮቼ ነገሩኝ ብሎ እንደጻፈው አንድነት ፓርቲ ውስጥ የተፈጠሩት አንጃዎች 99 በመቶ የእርቅ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በቅርቡም የእርቀ ሰላም ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ እንደ አዲስ አመራር ይመረጣል፡፡ በዚህ የእርቅ ጉባኤ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አቶ ስየ አብረሃ እና አቶ አንዷለም አራጌ እንደማንኛውም አባል በመራጭነትና በተመራጭነት መሳተፍ እንደሚችሉ መግባባት ላይ እንደተደረሰ ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ ሁኔታው እንደታሰበለት ከሄደ ህክምናቸውን በደቡብ አፍሪካ አጠናቀው ወደ አገርቤት የተመለሱትን የፓርቲውን መሥራች ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ወደ ፖለቲካ ለመመለስ ምቹ ኹኔታን እንደሚፈጥር ጋዜጣው ያለውን ግምት ገልጧል፡፡
No comments:
Post a Comment