Unity for Human Rights and Democracy is a volunteer based, not for profit community organization, striving to empower Ethiopian-Canadians to advocate for Human Rights,Democracy and Good Governance in Ethiopia.
Friday, December 18, 2015
Friday, November 27, 2015
በእዉቁ ከያኒ፤ደራሲ እና የኪነ-ጥበብ ሰዉ ደበበ እሽቱ Debebe Eshetu በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካኝነት "ኢትዬዽያ .. የባሩድ በርሜል" በሚል አርእስት ወደ አማርኛ የተተረጎመውን "Abyssinia . The Powder Barrel" መጽሐፍ ፊርማ እና ውይይት በአሻራ አርትስ አዘጋጅነት እሁድ ኖቬምበር 29 ቀን 2015 በታላቋ ቶሮንቶ ከተማ ይካሄዳል፡፡ እኛም በስነስርአቱ ላይ ለመካፈል እንዲሁም የናፈቀንን ወዳጃችን ጋሽ ደቤን በአካል ለማግኘት ጉዞ ወደ ቶሮንቶ ጀምረናል፡፡
"ውጥንቅጧ የወጣው የአሁኗ ኢትዬዽያን ሰለመፈጠሯ በ1935 ዓ.ም እንዴት እንደታስበ ለመረዳት ይህንን መጽሐፍ ማንበብ ወሳኝ ነው"
በዝግጅቱ ላይ መገኘት ለምትፈልጉ
Sunday, November 29, 2015 at Hirut Restaurant 2050 Danforth Avenue, starting from 5pm.
Friday, November 6, 2015
‹‹የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው›› አትሌት ከላሊ ንጉሴ አብርሃ
የረዥም ርቀት እና ማራቶን ሯጭ ሲሆን አሁን የሚገኘው በስደት ቶሮንቶ፣ ካናዳ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በነበረበት ወቅት ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ያሳለፈውን የህይወት ተሞክሮ በማስመልከት ከኢትዮጵ ዛሬ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፤ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
ኢ.ዛ.፡- በቅድሚያ ይህን
ቃለመጠይቅ እንድናደርግ ፈቃደኛ በመሆንክ በትዝታ ጋዜጣ ስም እያመሰገንኩ፤ እሰቲ እራስክን በማስተዋወቅ እንጀምር፡፡ የት
እንደተወለድክ ፣ ሙያህን እና የአስተዳደር ሁኔታክን ግለፅልኝ
አትሌት ከላሊ፡- ከላይ ንጉሴ
እባላለሁ፡፡ የተወለድኩት ራያ ከሚባል አካባቢ ሲሆን ትንሽዬ ገጠር ውስጥ ነው፡፡ እድገቴም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሲሆን እዛው
ራያ አካባቢ ነው፡፡ ትምህርቴንም ቢሆን እስከ ሁለተኛ ደረጃ እዛው ነው የጨረስኩት፤ በሙያ ደግሞ የረዥም ርቀት እና የማራቶን
ሯጭ ነኝ፡፡
ኢ.ዛ.፡-ትንሽ ስለ ራያ ህዝብ እና አካባቢው ብትነግረኝ?
አትሌት ከላሊ፡- ራያ የሚገኘው
በትግራይ ክልል ሲሆን፤ በህዝብ ቁጥር እንዲሁም በመሬት ይዞታው በክልሉ ደረጃ ሰፊ ነው ሊባል ይችላል፡፡ የራያ ህዝብ ዋነኛ
መተዳደያው በእርሻ ነው፡፡ ምንም እንኳን ሰፋ ያለ ይዞታ ቢኖረውም ህዝቡ ግን ከፍተኛ የሚባል በደል የደረሰበት ነው፡፡ ራያ በትግራይ
ክልል የተካለለ ቢሆንም የተገለለ አካባቢ ይመስላል፡፡ እንደሌሎቹ የትግራይ ግዛቶች የልማት እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ሊሆን
አልቻለም፡፡
ኢ.ዛ.፡- አካባቢው የልማት ተጠቃሚ
አይደለም ስትል ምሳሌ ልትጠቅስልኝ ትችላለክ?
አትሌት ከላሊ፡- ለምሳሌ በከተማ
እድገት ብንመለከት ማይጨው የራያ ዋና ከተማ ነው፡፡ እንደዋና ከተማነቱ ይኼ ነው የሚባል መሻሻል ወይም እድገት እንዲሁም
ለእድገቱ የሚያስፈልጉ ከመንግስት የሚደረጉ አቅርቦቶች የሉም፡፡ ሌሎች በትግራይ ክልል የሚገኙ አካባቢዎችን ብንመለከት ልዩነቱን
መገንዘብ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ ለመጥቀስ ያክል አዲግራት ወይም ኡቅሮ የሚባሉ አካባቢዎች በአማካይ አንድ አይነት የህዝብ ቁጥር
እና የመሬት ስፋት ይዘው ግን በመሀከላቸው ያለው የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ሰፊ ነው፡፡ አንድ መሰረተ ልማት
ብናነሳ እንኳን፣ ህክምናን ብንመለከት በራያ አካባቢ ማይጨው የሚባል ቦታ ላይ አንድ መካከለኛ የሚባል ሆስፒታል ነው
የሚገኘው፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረ ይኸው አሁን ከ20 አመት በላይ አሳልፏል፤ ራያን በሚያክል አካባቢ
አንድ ክሊኒክ ብቻ፣ አስበው ከተለያዩ የራያ ክፍሎች ሰው ታሞ የሚመጣው እዚችው ሀኪም ቤት፣ እዛ ድረስ እስኪደርስ ያለውን
እርቀት፣ መንገድ ላይ የሚሞትም አለ፣ እንደዛም ሆኖ ብትደርስ ብዙ ጊዜ ወደሌላ የትግራይ አካባቢዎች ለሚገኝ ሆስፒታል ሪፈር
ትደረጋለክ፡፡ የሌሎች አካባቢ እንቅስቃሴዎችን የማየት እድሉን ስላገኘው ከራያ ጋር ሳመዛዝነው ውስጤ ያዝናል፡፡ ይኼም ሳያንስ
መንግስት እንዲህ እና እንዲያ እያደረኩ ነው ብሎ በሚዲያ ሲናገር ጉዳዩን ለምናውቀው የሚያሳዝን ነው፡፡
ኢ.ዛ.፡-በቋንቋ
ስንመለከት ራያ በሦስት የተከፈለ ነው ብለው የሚናገሩ አሉ ይኸውም የአማርኛ ተናጋሪ፣ የኦሮምኛ እንዲሁም የትግርኛ ተናጋሪ፤
ሦስቱም አንድ ላይ ተጠቃለው ነው ወይስ እንደቋንቋቸው አካባቢያቸውም ይለያያል?
አትሌት ከላሊ፡- ራያን በአጠቃላይ
ስንመለከተው በሁለት ልንከፍለው እንችላለን፤ ይኸውም ራያ ቆቦ የሚባለው ወደ አማራ አካባቢ የሚገኘው ሲሆን በአብዛኛው የአማርኛ
ተናጋሪ ያለበት ክፍል ሲሆን፤ እኔ ወደምኖርበት አካባቢ ያለው ደግሞ ራያ አዘቦ የሚባለው አካባቢ ሲሆን ትግርኛ፣ አማርኛ
እንዲሁም ኦሮምኛም ተናጋሪዎች ያሉበት ነው፡፡ እንዲህ ቢከፋፈሉም ያው እንደ አንድ ክልል ነው የሚታወቁት፡፡
ኢ.ዛ.፡-ወደ አትሌቲክሱ
ህይወትክ እንመለስ እና እንዴት ወደ ሩጫው ገባህ?
አትሌት ከላሊ፡- ፕሮፌሽናል
የአትሌቲክስ ህይወት የጀመርኩት እዛው ራያ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ በጊዜው የከፍተኛ ሁለተኛ ተማሪ ነበርኩኝ ጊዜውም ወደ
1999 ዓ.ም. አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ በጊዜው ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ሯጮች በክልሉ በተካሄደው ውድድር ይሳተፉ ነበር፡፡
እኔም የምኖርበትን ወረዳ በመወከል ለመሳተፍ በቃሁ፡፡በጊዜው ጥሩ የሚባል ሰዓት በማስመዝገቤ ከዛን ጊዜ በኋላ በሌሎች
ውድድሮችም እንድሳተፍ ተደረኩኝ ማለት ነው፡፡
ኢ.ዛ.፡-እንደሚታወቀው
እትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በብዙ የሚቆጠሩ ወጣት አትሌቶችን ታፈራለች፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ ችሎታ ኖሯቸው እንኳን እድሉን
አግኝተው ወደ ከፍተኛ መድረኮች ወጥቶ ለመወዳደር በራሱ ትልቅ ፈተና እንደሚሆንባቸው በየጊዘው የሚሰማ ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ
አንተም ከእነሱ አንዱ እንደመሆንክ እንዴት እድሉን አገኝተክ ልትወጣ ቻልክ?
አትሌት ከላሊ፡- እርግጥ ነው
ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ተግዳሮቶች አሉበት፤ የኔም ጉዳይ ቢሆን እድል ተጨምሮበት እንጂ ሚናልባትም እዛው እቀር ነበር፡፡ ወረዳ
ላይ ከተሳተፍኩ በኋላ ሌሎች ውድድሮችም ላይ አመርቂ ውጤት በማስመዝገቤ የትግራይ ክልልን ወክዬ እንድሳተፍ ተደረኩኝ፡፡ ከዛም
ወደ አዲስ አዲስ አበባ በመምጣት ትግራይን ወክዬ ተወዳድሬያለሁ፡፡ በይበልጥ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2002/2003 ዓ.ም. ጥሩ
ፐርፎርማንስ አሳይቼ ነበር በዚህም የተነሳ ማረሚያ ለሚባል የስፖርት ክለብ ውስጥ ለመሮጥ በቃሁ፡፡ እዛ በነበርኩበትም ወቅት
በተለያዩ ውድድሮች ላይ የተሳተፍኩ ሲሆን ይኸውም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ በበርካታ መድረኮች ላይ ለመወዳደር ችያለሁ፡፡
ኢ.ዛ.፡-በተለያዩ ሀገራት
የመወዳደር እድል እንዳገኘክ ነግረኸኛል፤ እንዴት ነበር በግልክ ነው ወይስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመቻችቶልክ ነው?
አትሌት ከላሊ፡- በእርግጥ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው በውድድሩ ላይ እንድንሳተፍ የሚያደርገው፡፡ ይሁን እንጂ የምትወዳደርለትን ክለብ ወይም
ሀገርህን አልያም ደግሞ በግልቅ መሳተፍ ትችላለክ፡፡ ዋናው ነገር በቅርብ ጊዜያት የምታስመዘግበው ውጤት ይወስነዋል፡፡ ለምሳሌ
በረዢም ርቀቶች ላይ ስትሳተፍ ቢያንስ ጥሩ ሰዓት እና ከ1-7 ወይም እስከ 8ኛ ደረጃ ላይ የሚወጡት ሯጮች ቅድሚያ ያገኛሉ፡፡
ሀገር እንዲወክሉ ይደረጋል ማለት ነው፡፡
ኢ.ዛ.፡-ከኢትዮጵያ
አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በተያያዘ በርካታ መረጃዎችን እንሰማለን፤ ይኸውም እኩል የሆነ እድል ለሯጮች አይሰጥም፣ በሙስና
የተጨማለቀ ነው፣ በብሔር የተከፋፈለ ነው፣ ሯጮች በሀገር ውስጥ እድል ሳይሰጣቸው ለሌላ ሀግር እየሮጡ ውጤት እያመጡ ነው እና
የመሳሰሉ ቅሬታዎችን፤ ከዚህ አንፃር አንተስ የታዘብከው ወይም የደረሰብክ ነገር አለ?
አትሌት ከላሊ፡- በቅድሚያ
የሰማኸው መረጃ ትክክል መሆኑን እኔው እራሴ ላረጋግጥልክ እወዳለው፡፡ ያው በየጊዜው የምንመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ እንደው
በቅርቡ እዛ በነበርኩበት ጊዜ የተከሰተውን አንድ ጉዳይ ብነግርክ፤ የሴቶች የረጅም ሩጫ ተካሂዶ ነበር፡፡ ታዲያ ውጤት ያመጡትን
ይመርጣሉ ብለን እየጠበቅን 2ኛ ነው 3ኛ የወጣችውን ጥለው ውድድሩ ላይ አቋርጣ የወጣችውን ተወዳዳሪ መርጠዋል፡፡ እሷም ሄዳ
ውጤት አላመጣችም በውድድሩ 24ኛ ነበር የወጣችው፡፡ ይህ እንግዲህ እኔ በቅርቡ የታዘብኩትን ነው የነገርኩህ፡፡ ይህ የሚያሳየው
ፌዴሬሽኑ ምን ያክል በዝምድና፣ በሙስና፣ በብሔር እና በፖለቲካ አቋምህ እንደሚወሰን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት አትሌቲክሱ
አያድግም፣ ለታዳጊዎች እድል አይሰጡም ከዚህ የተነሳ ይኸው የድሮ ዝናውን እያጣ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ ብዙ ችግር አለበት፤ እውነተኛ
ነገር እየተሰራ አይደለም፡፡ የመወዳደር አቅም እና ችሎታ እያለክ፣ ውድድር አግኝተክ፣ ኢንቪቴሽን ወረቀት መጥቶልክ እንኳን
በውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ ብር ጉቦ መስጠት አለብክ፡፡ ይህን ደግሞ ማድረግ የሚችሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡
ኢ.ዛ.፡-እንደገለፅክልኝ ይህ የሚያሳየው
በፌዴሬሽኑ ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ችግር እንዳለ ነው፡፡ ታዲያ አትሌቶቹስ ይኼን እያዩ እንደው ዝም ብለው ያልፋሉ፤ ተሰባስበው
የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ ከዚህ አንፃር?
አትሌት ከላሊ፡- የአትሌቶች
ማህበር የተቋቋመ አለ፡፡ ሁሉንም አትሌቶች ያቀፈ ማለት ነው፡፡ ሰብሳቢዎቹም ትላልቅ የሚባሉ አትሌቶች ናቸው፡፡ በየጊዜው
ስብሰባ ይደረጋል፣ ችግሮች ይነሳሉ፣ መፍትሄ ተብሎ ይወራል ነገር ግን እስካሁን ምንም ሊፈጥሩ አልቻሉም፡፡ አሁንም ችግሮቹ
እንዳሉ ናቸው፡፡
ኢ.ዛ.፡-ፌዴሬሽኑ ከገዢው ፓርቲ ጋር በተያያዘ ባለው የፖለቲካ
ትስስር ሲታማ ይሰማል፡፡ ለምሳሌ የቴክኒካል ዳይሬክተሩ አቶ ዱቤ ጁሎ የኢህአዴግ አባል መሆናቸው በራሱ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳ
ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንተ ምን አስተያየት አለህ?
አትሌት ከላሊ፡- እውነቱን
ለመናገር ዳይሬክተሩ ብቻ ሳይሆኑ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው፡፡ ምንመ እንኳን
ፌዴሬሽኑ ከፖለቲካ ገለልተኛ አካል በመሆን መስራት ሲገባው አሁን ባለው ሁኔታ ግን ይህ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ከዚህም የተነሳ
ማናቸውንም ጥያቄዎችን ማንሳትም ሆነ ወደ በላይ አካል ማቅረብ በራሱ ከባድ ነው፡፡ አንደኛ ሁሉም የተሳሰሩ ስለሆኑ ምላሽ
አታገኝም፤ ድምፄን አሰማለሁ ያልክም እንደሆነ የፖለቲካ ታፔላ ተለጥፎብክ ሌላ ችግር ይደርስብካል፡፡
ኢ.ዛ.፡-አንተ እንደ አንድ አትሌት ለዚህ መፍትሄው ምንድነው
ትላለክ?
አትሌት ከላሊ፡- በርግጥ እኔ
ፖለቲካኛ ስላልሆንኩና ብዙ ፖለቲካ ስላማላውቅ እንዲህ ነው ብዬ ስፊ ትንተና ልሰጥህ አልችልም፡፡ ግን እርግጠኛ ሆኜ የምነግርክ
መንግስት ከአትሌቲክሱ ውስጥ ጣልቃገብነት ማቆም አለበት፡፡ አጠቃላይ የስርዓት ለውጥ ካልመጣ በፌዴሬሽኑ አካባቢ ብቻውን ለውጥ
ይመጣል ወይ የሚለው ነግር ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡ ግን በአትሌቲክስም ይሁን በሌላው የህይወት መስክ ወጣቱም፤ የሚቀጥለው
ትውልድም ይኼን ስርዓት በርትቶ መታገል አለበት ነው የምለው፡፡ ሌላ ምንም አማራጭ የለኝም፡፡
ኢ.ዛ.፡-በመጨረሻ እንደው ሌላ የምትጨምረው ወይም የምታስተላልፈው
መልዕክት ካለህ?
አትሌት ከላሊ፡- በይበልጥ ወጣቱ
የተወሰደበትን የእኩልነት እና የነፃነት መብቱን፣ ለእውነት እና ለማንነቱ መታገል አለበት፡፡ ሰው በድህነቱ በብሔሩ ወይም
በፖለቲካ አስተሳሰቡ ሲጨፈጨፍ ዝም ብሎ መመልከት ሳይሆን አንድ ሆኖ መታገል አለበት፡፡ ሁሉም በሚችለው አቅሙ ማለት ነው፡፡
ኢ.ዛ.፡-ስለሰጠሀን ቃለምልልስ እናመሰግናለን፡፡
አትሌት ከላሊ፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡
Tuesday, October 20, 2015
Eskinder Nega Wins 2015 PEN Canada One Humanity Award
Eskinder Nega wins PEN Canada One Humanity award at 36th International Festival of Authors
TORONTO, Oct. 19, 2015 – The Ethiopian journalist Eskinder Nega will receive PEN Canada’s One Humanity Award on the opening night of the 36th International Festival of Authors (IFOA 36). The award, valued at $5,000, is presented at PEN’s annual gala to a writer whose work transcends the boundaries of national divides and inspires connections across cultures.
Mr. Nega, an independent journalist, was arrested in September 2011 under the provisions of Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation for criticizing the detention of a prominent government critic, and disputing the government’s assertion that detained journalists were terror suspects. At his trial the judge reportedly accused Nega of using “the guise of freedom” to “attempt to incite violence and overthrow the constitutional order” through a popular revolt similar to those of the Arab Spring.Convicted on June 27, 2012, Nega was sentenced to 18 years in prison. In December 2012 the United Nations Working Group on Arbitrary Detention said the sentence violated free expression and due process rights under international law. The UN group called for his immediate release. On May 2, 2013, the Ethiopian Federal Supreme Court upheld both the conviction and the sentence.
Nega is one of eight journalists and bloggers currently jailed in Ethiopia under the Anti-Terrorism Proclamation, according to PEN International’s case list. Six others were released in July 2015 after being held for periods ranging from 16 months to four years under the same legislation.
Since its 2010 UN Universal Periodic Review (UPR), Ethiopia has repeatedly used its Anti-Terrorism Proclamation to arbitrarily arrest, prosecute, and imprison independent journalists and opposition activists. Ahead of Ethiopia’s 2014 UPR, a shadow report by PEN International and the Committee to Protect Journalists found the Proclamation overbroad and inconsistent with international law. The use of the Anti-Terror Proclamation to stifle the independent media has been condemned both by regional human rights bodies and the UN.
The Ethiopian government has arbitrarily imposed restrictions on the distribution of broadcast and print licenses, the content and editorial position of news outlets, the freedom of movement of journalists, the accreditation of international journalists, and domestic access to international broadcasts and Internet content.
Since 1992, government pressure has forced at least 75 independent publications, overwhelmingly from the Amharic language press, to close. Although a large number of private publications continue to operate, less than a handful of publications cover politics with a critical perspective. A high number of journalists have fled the country as a result of government persecution.
Photo credit: Lennart Kjorling
http://pencanada.ca/news/eskinder-nega-wins-2015-pen-canada-one-humanity-award/
Wednesday, August 19, 2015
Saturday, August 8, 2015
Monday, April 13, 2015
Sunday, January 25, 2015
ሰላማዊ ትግላችን በምርጫ ቦርድ ህገ-ወጥ ውሳኔና በአገዛዙ የኃይል ርምጃ አይቀለበስም! – በሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች ማህበር
በዛሬዉ ዕለት ጥር 17 ቀን፣ 2007 ዓ.ም. በተደረገዉ ሰላማዊ ሰልፍ፤ በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላትና ደጋፊዎች ላይ የደረሰዉን ዘግናኝ ድብደባ፣ እስርና እንግልት በጥብቅ እንቃወማለን። የመንግሥት አስተዳደር ወይም ህግ አለ በሚባልበት አገር እጅግ በጣም በሚዘገንን ሁኔታ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የደረሰው ድብደባ የተጀመረዉን ሰላማዊ ትግል ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም የታለመ ነዉ ብለን አናምናለን። አገዛዙ አንድነት ፓርቲን እንደ ባዕድ ወይም ጠላት በሚመስል መልኩ ታጣቂ ኃይሎችን በብዛት በማሠማራት በሠልፈኞች ላይ ድብደባና እንግልት ፈፅሞባቸዋል።አገዛዙ በተደጋጋሚ በህጋዊ ፓርቲዎች አመራር አባላትና ደጋፊዎች ላይ ግድያና ድብደባ አንዲሁም ዘረፋ በማድረግ መንግሥታዊ ዉምብድናዉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። አንድነት ከአሁን በፊትም ከፍተኛ መሥዋዕትነት እየከፈለ፣ እልህ አስጨራሽ መራር ሰላማዊ ትግሉን እየመራ ይገኛል። ህወሃት መራሹ አምባገነን የዘውግ መንግሥት በፈጠራቸዉ አሥመሣይ ተቋማት በመገልገል በእጅ አዙር በህዝቡና በሰላማዊ የተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ ውምብድና እየፈፀመ ይገኛል። ምርጫ ቦርድ፣ፖሊስና የደህንነት ኃይል፤እንዲሁም አሥተዳደሩ ባጠቃላይ አንድነትንና ሌሎች አጋር ፖርቲዎችን ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፉት ቆርጦ የተነሳ ይመስላል።
አገዛዙ ከህገ-ወጥ ተግባሩ ታቅቦ መንግሥታዊ ሥነ ምግባር እንዲዝና ሰላማዊ ፖርቲዎችን የማጥፋትና የማሳደዱን ክፉ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን። ይህ ካልሆነና የሰላማዊ ትግሉ በር ከተዘጋ ህዝቡ አማራጭ መፍትሄ መፈለጉ ስለማይቀር ለሚፈጠረዉ አገራዊ ቀዉስ የስርዐቱ ኀላፊዎች ተጠያቂ እንደሚሆኑ አንጠራጠርም።
በመጨረሻም የአንድነት አመራሮች የአካሄዱትን ፍፁም ሰላማዊ ሰልፍ አድናቆታችንን እየገለጽን፤ ይህን ዘግናኝ ግፍና በደል ለማስቆም፣ እንዲሁም የአገዛዙን አፈናና ጭቆና ለመቋቋም፣ ብሎም የህዝቡን ልዕልና ለማስከበር ኢትዮጵያዉያን ከመቼዉም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ተደራጅተዉ በመታገል በህዝባዊ ኃይል አገዛዙን ከማስወገድ በስተቀር ሌላ አማራጭ የለም። ስለሆነም ትግላችንን በህብረት አጠናክረን ህዝባዊ ትግሉን ለማቀጣጠል ሁላችንም ቆርጠን እንነሳ፦
በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚደረገዉ ድብደባና ግድያ በአስቸኳይ ይቁም!
ህዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
የኢትዮጵያ ህዝብ ያሸንፋል!
በሰሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶች ማህበር
የሥራ አመራር ቦርድ
Saturday, January 17, 2015
ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!!
ጉዳዩ፥ በቅርቡ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በተመለከተ፡፡
እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከምርጫ ቦርድ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ በ 4 ቀን ውስጥ እንዲጠራና የፓርቲውን መሪ በድምፅ አሠጣጥ መመሪያው መሠረት እንዲመርጥ ስለተገደደ አንድነት ፓርቲም በሆደ ሰፊነት በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ ባያምንበትም ሕግ ለማክበርና የሠላማዊ ትግሉን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ስለሚረዳ በሌለ አቅሙ በ 4 ቀን ውስጥ በአስቸኳይና በታላቁ በገና በዓል ሣምንት የጉባዔ አባላትን ከክ/ሃገር ጭምር ጉባዔ ጠርቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፋ በ 4 ቀን ጉባዔ እንዲጠራ ካዘዘ በኋላ በጉባዔው ተገኝቶ ምርጫውን ታዝቦ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጋብዞ ሣይገኝ ቀርቷል፡፡ ይህ ዓይነት የምርጫ ቦርድ ሕገ-ወጥነት በጥብቅ ሊወገዝ ይገባል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው ምርጫ ቦርድ አሁንም እጅግ በጣም በሚያሳፍርና ይሉኝታ በሌለው አካሄድ አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በድጋሜ ጉባዔ እንዲጠሩ ሕገ-ወጥ ትዐዛዝ ለማስተላለፍ ችሏል፡፡ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ውስጥ ጉዳይ የመፈትፈት፣ ውሣኔ የመቀልበስ፣ እንዲሁም የፓርቲዎችን አመራር የማፅደቅ ወይም ያለማጵደቅ መብት ጨርሶ ሊኖረው አይገባም፡፡ ምከንያቱም እንደዚህ ዓይነት ጣልቃ ገብነት ካለ የፓርቲዎች የበላይ አካል የሚሆነው የአባሎቻቸው ጠቅላላ ጉባዔ ትርጉም አልባ ይሆናልና፡፡
አንድነት ፓርቲ በምጫ ቦርድ በድጋሜ የተላለፈውን ጉባዔ የመጥራት ትዕዛዝ እንደማይቀበለው መግለፁን ስንቀበል፤ እኛም የአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር ሙሉ በሙሉ እንደምንደግፍ እናረናገግጣለን፡፡ ምርጫ ቦርድ እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ለአገዛዙ ወገናዊነትን ለማረጋገጥ በአስተዳደሩ ኃላፊዎች በመታዘዝ፤ በአንድነት ፓርቲና በሌሎች ተቃዋሚ አጋር ፓርቲዎች
የሚያደርገውን ሕገ-ወጥነት አስተዳደራዊ ክፉ ሥራ አጥብቀን እንቃወማለን! አንቀበለውም:: አገዛዙ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ከፈለገ ህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎችን በህገ-ወጥነት ሣይሆን በስርዓት፣ በአግባቡ የጨዋታ ሜዳውን ክፍት ማድረግ አለበት፡፡ የምርጫ ቦርድ የተደጋጋሚ ጉባዔ ጥሩ ትዕዛዝ ህገወጥ ነው፡፡ ተቀባይነት የለውም፡፡ አገዛዙ እንደዚህ ዓይነት እጅግ የዘቀጠ ፀያፍ ስራ
ውስጥ ተነክሮ ያለው መጪውን ብሔራዊ ምርጫ ያለተቀናቃኝ ብቻዉን ተወዳድሮ ለማሸነፍ ካለው ጭፍን ፍላጐት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ሆኖም ግን ይህ አካሄዱ ሃገሪቱን ወደ ባሰ ምስቅልቅል ይወስዳታል እንጅ ሌላ ፋይዳ የለውም፡ በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ማለትም መኢአድ፣ ሰማያዊ፣ መድረክና፣ ሌሎችም ፓርቲዎች ተቀራርበው ትግሉን በጋራ እንዲመሩት ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ፓርቲዎቹ አገዛዙን በመቃወም ለሚያደርጓቸው ማንኛውም የሠላማዊ እንቅስቃሴዎች ከጐናቸዉ እንደምንቆም በዚህ እጋጣሚ ማሣወቅ እንወዳለን፡፡ አንድነት ፓርቲ በሚያደርጋቸው የትብብር ጥሪዎችና የአመራር ስልቶች በተናጠልም ወይም ከሌሎች አጋር ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርጋቸው ትግሎች ሙሉ በሙሉ የማቴሪያልና የሞራል ድጋፍ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብም የአገዛዙን ተንኮል በመረዳት ከአንድነትና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጐን በመሰለፍ የነፃነት ትግሉ እንዲያፋጥን ጥሪ አናቀርባለን፡፡
ጉዳዩ፥ በቅርቡ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና በአንድነት ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ በተመለከተ፡፡
እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ባለፈው ሣምንት ከምርጫ ቦርድ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጠቅላላ ጉባዔ በ 4 ቀን ውስጥ እንዲጠራና የፓርቲውን መሪ በድምፅ አሠጣጥ መመሪያው መሠረት እንዲመርጥ ስለተገደደ አንድነት ፓርቲም በሆደ ሰፊነት በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ ባያምንበትም ሕግ ለማክበርና የሠላማዊ ትግሉን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ስለሚረዳ በሌለ አቅሙ በ 4 ቀን ውስጥ በአስቸኳይና በታላቁ በገና በዓል ሣምንት የጉባዔ አባላትን ከክ/ሃገር ጭምር ጉባዔ ጠርቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፋ በ 4 ቀን ጉባዔ እንዲጠራ ካዘዘ በኋላ በጉባዔው ተገኝቶ ምርጫውን ታዝቦ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጋብዞ ሣይገኝ ቀርቷል፡፡ ይህ ዓይነት የምርጫ ቦርድ ሕገ-ወጥነት በጥብቅ ሊወገዝ ይገባል፡፡ ይህ አልበቃ ብሏቸው ምርጫ ቦርድ አሁንም እጅግ በጣም በሚያሳፍርና ይሉኝታ በሌለው አካሄድ አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በድጋሜ ጉባዔ እንዲጠሩ ሕገ-ወጥ ትዐዛዝ ለማስተላለፍ ችሏል፡፡ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ውስጥ ጉዳይ የመፈትፈት፣ ውሣኔ የመቀልበስ፣ እንዲሁም የፓርቲዎችን አመራር የማፅደቅ ወይም ያለማጵደቅ መብት ጨርሶ ሊኖረው አይገባም፡፡ ምከንያቱም እንደዚህ ዓይነት ጣልቃ ገብነት ካለ የፓርቲዎች የበላይ አካል የሚሆነው የአባሎቻቸው ጠቅላላ ጉባዔ ትርጉም አልባ ይሆናልና፡፡
አንድነት ፓርቲ በምጫ ቦርድ በድጋሜ የተላለፈውን ጉባዔ የመጥራት ትዕዛዝ እንደማይቀበለው መግለፁን ስንቀበል፤ እኛም የአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር ሙሉ በሙሉ እንደምንደግፍ እናረናገግጣለን፡፡ ምርጫ ቦርድ እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ ለአገዛዙ ወገናዊነትን ለማረጋገጥ በአስተዳደሩ ኃላፊዎች በመታዘዝ፤ በአንድነት ፓርቲና በሌሎች ተቃዋሚ አጋር ፓርቲዎች
የሚያደርገውን ሕገ-ወጥነት አስተዳደራዊ ክፉ ሥራ አጥብቀን እንቃወማለን! አንቀበለውም:: አገዛዙ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ከፈለገ ህጋዊ የፓለቲካ ፓርቲዎችን በህገ-ወጥነት ሣይሆን በስርዓት፣ በአግባቡ የጨዋታ ሜዳውን ክፍት ማድረግ አለበት፡፡ የምርጫ ቦርድ የተደጋጋሚ ጉባዔ ጥሩ ትዕዛዝ ህገወጥ ነው፡፡ ተቀባይነት የለውም፡፡ አገዛዙ እንደዚህ ዓይነት እጅግ የዘቀጠ ፀያፍ ስራ
ውስጥ ተነክሮ ያለው መጪውን ብሔራዊ ምርጫ ያለተቀናቃኝ ብቻዉን ተወዳድሮ ለማሸነፍ ካለው ጭፍን ፍላጐት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ሆኖም ግን ይህ አካሄዱ ሃገሪቱን ወደ ባሰ ምስቅልቅል ይወስዳታል እንጅ ሌላ ፋይዳ የለውም፡ በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ማለትም መኢአድ፣ ሰማያዊ፣ መድረክና፣ ሌሎችም ፓርቲዎች ተቀራርበው ትግሉን በጋራ እንዲመሩት ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ፓርቲዎቹ አገዛዙን በመቃወም ለሚያደርጓቸው ማንኛውም የሠላማዊ እንቅስቃሴዎች ከጐናቸዉ እንደምንቆም በዚህ እጋጣሚ ማሣወቅ እንወዳለን፡፡ አንድነት ፓርቲ በሚያደርጋቸው የትብብር ጥሪዎችና የአመራር ስልቶች በተናጠልም ወይም ከሌሎች አጋር ፓርቲዎች ጋር ለሚያደርጋቸው ትግሎች ሙሉ በሙሉ የማቴሪያልና የሞራል ድጋፍ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብም የአገዛዙን ተንኮል በመረዳት ከአንድነትና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጐን በመሰለፍ የነፃነት ትግሉ እንዲያፋጥን ጥሪ አናቀርባለን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)