Friday, October 28, 2016

የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት እንዲከበር ግፊትን እንዲያደርግ ተጠየቀ
ኢሳት (ጥቅምት 18 ፥ 2009)
የካናዳ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ልማታዊ ትብብር በመጠቀም በሃገሪቱ ዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት እንዲከበር ግፊትን እንዲያደርግ የካናዳ የፓርላማ አባላት ጠየቁ።
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ወደ 1ሺ 600 አካባቢ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ያወሱት የፓርላማ አባላቱ የካናዳ መንግስት ማንኛውንም አማራጭ በመጠቀም እርምጃ እንዲወስድ ፒተር ኪንግ የተባሉ የፓርላማ አባል አሳስበዋል።
ለሃገራቸው መንግስት የጽሁፍ መልዕክትን ያቅረቡት የፓርላማ አባሉ፣ ካናዳ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ ለዴሞክራሲ መከበር ስትል ተጽዕኖን ለማድረግ በአማራጭነት መመልከት እንደሚገባት ጠይቀዋል።...
“ሁሉም ኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነቱ ተጠብቆ መኖር ይኖርበታል” ሲሉ በጽሁፋቸው ያመለከቱት ፒተር ኬንት በህግ የበላይነት የሚያምን መንግስት ብቻ ይህንን ስርዓት ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሚችል አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረት አዋጁ የሰብዓዊ መብት ረገጣን ያባብሳል ሲሉ ስጋታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።
አሜሪካ በተለየ መልኩ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ማሳሰቢያን የሰጠች ሲሆን፣ የሃገሪቱ ዕርምጃ በሌሎች አለም አቀፍ አካላት ዘንድ ስጋት መፍጠሩ ይነገራል።
መቀመጫቸውን በካናዳ ያደረጉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ዕርምጃን መውሰድ ይኖርበታል ሲሉ ዘመቻ ሲያካሂዱ መቆየታቸውን CBC የተሰኘ የሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ከሽብርተኛ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለእስር ተዳርጎ የሚገኝ አንድ ካናዳዊ ለማስለቀቅ የካናዳ መንግስት ማንኛውንም ጫና ማድረግ እንዳለበት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማቱ በመጠየቅ ላይ ናቸው።
ባሽር ማክታል የተባለው ካናዳዊ ወደ ሶማሊያ ባቀና ጊዜ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውሎ በሽብርተኛ ወንጀል ክስ የእድሜ ልክ ዕስራት እንደተላለፈበት ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና የሃገሪቱ የፓርላማ አባላትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ጫናን በማሳደር ግለሰቡ እንዲለቀቅ የሚተየቅ ዘመቻን እያካሄዱ እንደሆነ ታውቋል።

MP urges Canada to call on Ethiopian regime respect human rights
ESAT News (October 28, 2016)
A member of the House of Commons of Canada urged his government to monitor the crises in Ethiopia with concern and ensure human rights are protected in the east African country.
...
“While there is a lot that’s unknown at this point regarding what is happening in Ethiopia, Canada should monitor the situation with concern,” Alexander Nuttall said addressing the Parliament.
The MP, who also briefed the parliament on the state of emergency and other measures taken by the Ethiopian regime restricting basic rights, urged his government to call on the Ethiopian regime human rights are protected. “As members of parliament in Canada, we need to call on the Ethiopian government to ensure freedom, democracy and human rights are protected in the region,” Nuttall said.
“Our thoughts and prayers are with the people of Ethiopia.”
Ethiopian Canadians, the Ethiopian Canadian Task Force for Democracy and the Ethiopian Advocacy Network have been campaigning for Canada, as one of the allies of the Ethiopian regime, to use its leverage to stop human rights violations in Ethiopia.
(Alexander Nuttall, https://www.facebook.com/AlexNuttallMP/videos/1209003089142865/ 

No comments: